በምሁርና አክሊል ወረዳ ኢዜማ እያደረገ ላለው የምርጫ 2013 ዘመቻ ድጋፍ
Fundraising campaign by
Muhir Aklil EZema Support
-
US$10.00raised of $2,000.00 goal goal
The campaign owner has stopped the page from accepting further donations. Please contact them if you'd still like to donate
Campaign Story
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በመጨው ምርጫ 2013 በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ህዝብ በየዘርፉ የገጠሙት ተግዳሮቶች በሚመለከተው አካል በትክክል ተሰምተው እንዲፈቱ አይነተኛ ድምጽ የሚሆኑ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤትና የክልል ም/ቤት እጩዎችን አቅርቧል። ለዘመናት እዚያው ጉያው ስር ሆነው ህዝቡን በሙያቸውና በእውቀታቸው እያገለገሉ የቆዩት የኢዜማ እጩዎች አያደረጉት ባሉት የምረጡኝ ዘመቻ ለሚያስፈልጋቸው እንቅስቃሴና ወጪ የበኩልዎን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ በትህትና እንጠይቃለን።
በአገራች ብዙ ቦታዎች በሆነው መልኩ በምሁርና አክሊል ወረዳም እንዲሁ የገዥው ፓርቲ እጩዎች ብዙ የመንግስት ቁሳቁስና መጓጓዣን ጭምር በመጠቀም ቅስቀሳ ማድረግ እንደሚችሉ ይታወቃል። በአንጻሩ የኢዜማ እጩዎች የምርጫ ዘመቻውን የሚደጉሙት በአብዛኛው በግለሰብ ደረጃ ከሚያገኙት የወር ደመወዝ እንዲሁም ከአርሶ አደሩ ከሚሰበሰብ አነስተኛ መዋጮ ነው። በመሆኑም የምርጫውን ዝግጅት ፍትሐዊ በማድረግ የማህበረሰቡን ችግሮች ለመፍታት በሚጠቅም መልኩ የተጀመረውን ዴሞክራሲያዊ የሐሳብ ፉክክር የሚያነቃቃ መጠነኛ ድጋፍ ማድረግ ያስፈልጋል።
ለሀገራችንም ሆነ ለወረዳችን ወሳኝ በሆነው በዚህ ምርጫ በወረዳችን ተወላጆች ለኢዜማ የሚደረግ አስተዋጽኦ ትልቅ ታሪካዊ ትርጉም ይኖረዋል። ይህንን በማድረግ በሚፈለግ ጊዜ ከማህበረሰቡ ጎን በመቆምዎ የምሁርና አክሊል ወረዳ የኢዜማ አባላትና ደጋፊዎች በመራጩ ህዝብ ስም ከወዲሁ ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
Organizer
- Muhir Aklil EZema Support
- Campaign Owner
No updates for this campaign just yet
Donors & Comments
- Anonymous
- Donated on Apr 11, 2021